ንስሐ ጸሎት ለኢትዮጵያ

መጋቢት 5 2015 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ይህ ጸሎት የተዘጋጀው የሚከተሉትን ነጥቦች ተመርኩዞ ነው፦ ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ 11 እንግዲህ አምላክህን እግዚአብሔርን ውደድ፥ ሕጉንም ሥርዓቱንም ፍርዱንምትእዛዙንም ሁልጊዜ ጠብቅ። ኦሪት ዘፀዓት መዕራፍ 195 ፤ አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብሁሉ የተመረጠ ርስትትሆኑልኛላችሁ፤ ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 14 15፤ ብትወዱኝContinue reading “ንስሐ ጸሎት ለኢትዮጵያ”

የክርስቶስ ጎን በመስቀል

በመስቀሉ ላይ ክርስቶስ ለሚያምኑና ወደ እርሱ ለሚመጡት ሁሉ ውሃና ደምን ለማውጣት ጎኑን በጦር ተወጋ:: ውሃው የኃጢአትን ርኩሰት ለማጠብ ደሙ ደግሞ የኃጢአትን ኃይል ለመከላከል። ኃጢአተኛው በውስጡ ጽድቁን ፣ ቅድስናውን እና ቤዛነቱን እንዲያገኝ የክርስቶስ ጎን በመስቀል ላይ የተከፈተበት ቀን ምነኛ የተባረከ ነው::

አቤቱ መልሰን ፊትህንም አብራ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ሕዝቤ ሆይ ሕጌን አድምጡ ጆሮአችሁንም ወደ አፌ ቃል አዘንብሉ:: መዝሙረ ዳዊት 77(78): 1 በዚህ መዝሙር ላይ ምንም እንኳን እግዚአብሔር እስራኤልን ከግብፅ ምድር የሚደንቁ ተአምራትን አድርጎ ቢያስወጣቸውም ከወጡም በኃላ ይህ ተአምራት በተለያየ መልክ ቢቀጥልም እስራኤል ግን እግዚአብሔርን አልሰማም:: መዝሙረ ዳዊት 77(78) ቁጥር  32 ላይ “ከዚህም ጋር  እንደገና በደሉContinue reading “አቤቱ መልሰን ፊትህንም አብራ”

ኢተፈጥሮአዊ ፣ ተፈጥሮአዊ እና ልዕለ ተፈጥሮአዊ የአይነ ልቦና ድርጊት

ቅዱሳን አባቶች የተለያዩ የመንፈሳዊ ሕይወት ገጽታዎችን ሁሉ በየዘመናቱ አስተናግደዋል፡፡ እናም የአይነ ልቦና መታወር ርዕሰ ጉዳይ የሰውን ልጅ ህመም እና ፈውስ በተመለከተ በጣም አስፈላጊ ከሆኑት መካከል ስለሆነ እነርሱም ስለዚህ ረዕስ ብዙ ብለዋል። ቅዱስ ማርቆስ የአይነ ልቦናን ሁኔታ በሦስት መልኩ ያስቀምጠዋል እነርሱም ከተፈጥሮ ከፍ ያለ(ልዕለ ተፈጥሮአዊ) እና ከተፈጥሮ ጋር ተቃራኒ የሆነው(ኢተፈጥሮአዊ) እና ተፈጥሮአዊ ናቸው። አንድ ሰው የእግዚአብሔርንContinue reading “ኢተፈጥሮአዊ ፣ ተፈጥሮአዊ እና ልዕለ ተፈጥሮአዊ የአይነ ልቦና ድርጊት”

ለሞቱት ሰዎች ማዘን ወይስ?

አንድ ልጅ ሲወለድ ምን ኃጢአት እንደሚጠብቀው ስለማያውቅ ያለቅሳል፡፡ አንድ ሰው ሲሞት ግን ወደ ዘላለማዊ ሕይወት ስለገባ ደስተኛ ነው፡፡ በዙሪያው ያሉት ሁሉ ግን በዚህ ምድር ላይ መቆየት ስላለባቸው ያለቅሳሉ፡፡ ለሞቱት ሰዎች እጅግ ማዘን አያስፈልግም ፣ በወንጌል ላይ ጌታ ቃል የገባውን የመኖሪያ ቤት እንዲሰጣቸው ወደ ጌታ መጸለይ ይሻላል፡፡ ሀዘን ሁሉንም ነገር ያጠፋል፡፡ ከጌታ የተቀበሉትን ሰላም ያጠፋል፡፡ በእረፍትContinue reading “ለሞቱት ሰዎች ማዘን ወይስ?”

ስምንቱ ክፉ ስሜቶች ወይም ሐሳቦች

ቅዱስ ካሲያን እንደሚለው ስምንት ክፉ ሐሳቦች አሉ። እነርሱም ከመጠን በላይ መብላት (ሆዳምነት) ፣ ወሲባዊ ብልሹነት (ብልግና) ፣ ከፍተኛ ስግብግብነት ፣ ኃይለኛ የመበሳጨት ስሜት (ቁጣ) ፣ ተስፋ መቁረጥ (ድብርት) ፣ ግድየለሽነት ፣ ለራስ ከፍ ያለ ግምት መስጠት (በራስ መተማመን)  እና ትዕቢት (ኩራት) ናቸው። ከስምንቱ ክፉ ስሜቶች ጋር የሚዛመዱት እነዚህ ስምንት ክፉ ሀሳቦች እንዴት ይድናሉ? 1. ከመጠንContinue reading “ስምንቱ ክፉ ስሜቶች ወይም ሐሳቦች”

ቅዱሳን አበው ስለ ሲኦል ምን አሉ?

ቅዱስ አባ እንጦንስ እግዚአብሔር ቸር ከስሜት ተጸዕኖ የተላቀቀ የማያዳላ ከጊዜ በኃላ የማይለወጥ ነው፡፡ እግዚአብሔር መልካም በሚያደርጉ ሰዎች ላይ የሚደሰት እና እሱን ለሚያከብሩ ምህረትን የሚያደርግ ፣ በአንፃሩ ደግሞ በክፉ መንገድ የሚሄዱና በኃጢያት በወደቁ ሰዎች ላይ ፊቱን የሚያዞር ከሆነ አንድ ሰው እንዴት እግዚአብሔር የማይለወጥ ምክንያታዊ እና የማያዳላ ነው ብሎ ሊያስብና ሊናገር ይችላል?  ለዚህ መልሱ እግዚአብሔር ደስ አይለውምContinue reading “ቅዱሳን አበው ስለ ሲኦል ምን አሉ?”