እኔ ግን እላችኋለሁ ፣ ጠላቶቻችሁን ውደዱ ለሚጠሉአችሁ መልካም አድርጉ ለሚያሳድዱአችሁ ጸልዩ፡፡ (ማቴዎስ 5: 44) ለምንድነው ይህንን ያዘዘው? ከጥላቻ ፣ ከመበሳጨት ፣ ቁጣ እና ቂም ፣ ነፃ ያወጣችሁ ዘንድ ፣ እንዲሁም ሁሉንም የሚወደውን የላቀ ስጦታ የሆነውን ለፍጹም ፍቅር ብቁ እንድትሆኑ ነው። እግዚአብሔርን በመምሰል ሁሉንም ሰዎች እኩል መውደድ ካልተቻለ እንደዚህ ዓይነቱን ፍቅርን ማግኘት አትችሉም። እግዚአብሔር ሰዎችን ሁሉ በእኩል ይወዳል እናም ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲመጡ ይመኛል። (1 ጢሞቴዎስ 2: 4)
እኔ ግን እላችኋለሁ ፣ ክፉን አትቃወሙ ፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው በቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ቢመታህ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት። ማንም ሰው በፍርድ ሸንጎ ፊት እጀ ጠባብህን ለመምውሰድ ከፈለገ ፥ ልብስህንም ተውለት። አንዱ ኪሎ ሜትር እንድትሄድ ለሚያስገድድህ ማንኛውም ሰው ሁለት ኪሎ ሜትሮችን አብረህው ሂድ። (ማቴዎስ 5: 39-41) ለምን እንዲህ አለ? ከቁጣ እና ከመበሳጨት ነፃ ያደርግህ ዘንድ እንዲሁም በአንተ መቻልና ትዕግስት ሌላውን ሰው ለማረም ሲሆን እንደ መልካም አባት ሁለታችሁንም በፍቅር ቀንበር ስር ያገባችሁ ዘንድም ነው፡፡
ክርስቶስ በመካከላችን ነው
ለዘላለሙም ይሆናል
ዮናስ አሰፋ (አስበ ፃድቅ) ነኝ
ነሐሴ 06, 2012 (Aug 12, 2020)
ከምንጭ መስክ
ቨርጂኒያ