እግዚአብሔርን ለማየት ከፈለግን መንገዱ ቀላል ነው ፡፡
1 ኛ የቤተክርስቲያንን ምስጢራትን (ንስሀ እና ቁርባን) በሕይወታችን መተግበር፡፡ ምስጢር ብለን የምንጠራቸው አለምክንያት አይደለም፡፡ እነዚህ ምስጢሮች ወደ እራሱ ወደ እግዚአብሔር የሚያደርሱንና የሚያዋህዱን ስለሆነ ነው፡፡ እግዚአብሔር ረቂቅ ስለ ሆ ነ በምክንያታዊነት እና በአእምሮ ሊታወቅ አይችልም።
2 ኛ ሰው ላይ መፍረድ አቁም ፡፡ የምትለው ትክክል ቢሆንም እንኳን በባልንጀራህ ላይ ያለውን ችግር ወይም ስህተት መለየትና ጣት መቀሰር አቁም፡፡ ብዙ ጊዜ ፣ ስህተት የሆነውን ነገር በመለየት ትክክል ረገድ ትክክል ነን ፡፡ እነሱ ያንን ማድረግ የለባቸውም ወይም እንደርሱ ማለት የለባቸውም እንላለን ፡፡ ወይም ለእነርሱ እንደዚህ ማድረጋቸው ወይም ያንን ማድረጋቸው መጥፎ ነው እንላለን ፡፡ ችግሩ እኛ ተሳስተን አለመሆናችን ነው ፡፡ ችግሩ ይህ አካሄድ ልባችንን የሚመርዝ መሆኑ ነው ፡፡ ይህ ዓይነቱ እውነት ይገድለናል ፡፡ ክርስቶስ ያንን በጣም ግልፅ አድርጎታል፡፡ መፍረድ አቁም እና ልብ ነፃ ይሁን፡፡ እግዚአብሔር የሰጠንን ነገሮችን የማናይበት ምክንያት ስላልተሰጠንና ከእኛ ስለራቁ አይደለም ፣ ማየት ያልቻልንበት ምክንያት ልባችን በፍርድና በመኮነን ስለተሞላ አይነልቦናችን ስለተሸፈነ ነው፡፡ እነዚህን ሁለት ነገሮች ብቻ ካደረግን ፣ እግዚአብሔርን ከአእምሮ በላይ በሆነና በሚገርም መልኩ እናያዋለን፡፡
ሰላም ለሁላችን
ዮናስ አሰፋ (አሰበ ፃድቅ) ነኝ
ሐምሌ 26, 2012
ከምንጭ መስክ
ቨርጂኒያ