ይህ የራዕይ ሰነድ ለአጥቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ይሆናል በሚል በምሳሌነት የተዘጋጀ ነው ማንኛውም ተቋም የራዕይ ሰነድን ጸሎትን ተንተርሶ ከአስተዳዳሪዎችና ከአባላቱ ጋር በገልጽ በመነጋገርና በመመካከር ቢያዘጋጅ በልምድና በግብታዊነት ከመጓዝ ይድናል። ይህንን ለሚመለከቱ ሁሉ ልዑል እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድላቸው።
ራዕይ (Vision) ምን ማለት ነው?የተለያየ መልስ ሊኖረው ይችላል እንዴትስ ይመጣል? እንዴትስ ይሰጣል?የራሱ የሆነ የተለያየ መልስ ይኖረዋል በአጭሩ ግን ራዕይ ማለት ዛሬ ላይ ሆኖ ነገን ማየት መቻል ነው በሌላ አነጋገር አንድ ተቋም ለወደፊቱ መሆን የሚፈልገው ማየት ማለት ነው። ተልእኮ መግለጫ (Mission Statement) አንድ ተቋም አሁን ምን ቢያደርግ ራዕዩን ለማሳካት የአቋም መግለጫ ነው፡፡ እግዚአብሔር የራዕይ አምላክ ነው። አንድ ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል ለእስራኤል የሰጠውን ስንመለከት እስራኤልን ከግብፅ ባርነት አውጥቶ ማርና ወተት ወደምታፈሰው የተስፋይቱ ምድር እንደሚያስገናቸው የሰጣቸው ራዕይ ነው
ይህም በኦሪት ዘጸአት ምዕራፍ 3 ቁጥር 17 ላይ እንዲህ ሲል ይገልፀዋል “ከግብፅም መከራ ወደ ከነዓናውያን ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ያቡሳውያንም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስስ አገር አወጣችኋለሁ አልሁ ብሎ ተገለጠልኝ በላቸው።” ወዴት መሄድ እንዳለብን እግዚአብሔር ራዕይ ቢሰጠንም መቼና በምን አይነት መንገድ የሚለውን ግን በአብዛኛው በእምነት ላይ የተመሠረተ ይሆናል በመሆኑም ሰው እግዚአብሔር በሰጠው አእምሮ እየተጠቀመ ይሻላል በሚለው መንገድ እግዚአብሔርን በመማለድ የሚችለውን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅበታል
ራዕይ ሕልም ነው ነገን በተሻለ ሁኔታ ማሰብ ነው ይህንን ትንሽ ለማብራራት ያህል አንዲት ታሪክ ላጫውታችሁ ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ሰው በግንባታ ቦታ ሲያልፍ አንድ ነገር ታዘበ ሦስት ሰዎች ቁጭ ብለው ለሕንፃ ግንባታ የሚውለውን ድንጋይ ሲጠርቡ ይመለከታል ሦስቱም የሚሰሩት ስራ አንድ አይነት ነው የሚጠቀሙበትም መሣሪያ አንድ አይነት ነው ነገር ግን ፊታቸው ገፅታ ላይ የተለያየ ስሜት እንዳላቸው ያስታውቅ ነበር የመጀመሪያው ሰውዬ ፊቱ ላይ የመናደድና የመሰላቸት ስሜት ይታይ ነበር ወንድሜ ሆይ ምን እያደረግህ ነው ብሎ በትሕትና ጠየቀው ጠራቢውም ቀና ብሎ እንኳን ሳያየው ምኑን ትጠይቀኛለህ አሰልቺ የሆነው ሥራዬ ለግንባታ የሚሆነውን ድንጋይ እየጠረብኩ ነው ይለዋል በመቀጠልም ሁለተኛውን ጠራቢ ይህንኑ ጥያቄ ይጠይቀዋል ሁለተኛው ጠራቢ የደስታ ምልክት ፊቱ ላይ የሚታይበት ሲሆን ፈገግ እያለ የሚሠራው ሥራ እያስደሰተው እንደሆነ ያስታውቅ ነበር ጠራቢውም አጥር እየሠራሁ ነው ሲል መለሰ ሰውዬውም ዞር ብሎ ቢያይ የተጀመረ አጥር አላየም ወደ ሦስተኛውም ሰው ሄዶ ይህንኑ ጥያቄ አቀረበለት ይህም ሰው ፊቱ ላይ እጅግ ደስታ ከመነበቡም በላይ ሥራውን የሚሠራው እየዘፈነ ነበር ለሥራውም ትልቅ ክብር እንዳለው ከሁኔታው ያስታውቅ ነበር እያንዳንድዋንም ደቂቃ ይጠቀምባት ነበር ሦስተኛውም ጠራቢ መለስ ብሎ በፈገግታ ተሞልቶ ታላቁን ካቴድራል እየገነባሁ ነው ብሎ መልስ ሰጠ
ለምንድነው እነዚህ ሦስት ጠራቢዎች የሚሠሩት ሥራ አንድ ሆኖ ሳለ ሀሳባቸው የተለያየው?ምክንያቱም እያንዳንዳቸው የሚፈልጉትን ነገር በአይነ ሕሊናቸው ማየት በመቻላቸው ነው አስተያየታቸውም የፈጠረው ራዕይ የተለያየ እርካታን ፈጥሮባቸዋል የመጀመሪያው ጠራቢ በሥራው ላይ ምንም አይነት ዓላማና ግብ ባለማየቱ ምክንያት ሥራውን አሰልቺ ከማድረጉም በላይ ሥራውንም ጥሎ የመሄድ እድል ሰፊ ነበር ሁለተኛው ግን የሥራው ውጤት ምን ላይ እንደሚውል በማሰቡ በመጠኑም ቢሆን ደስተኛ እንዲሆን አድርጎታል ሦስተኛው ግን ይህ የድንጋይ ጥርብ ካቴድራል እንደሚሠራባት በማየቱ በሥራው በጣም ደስተኛ እንዲሆን አድርጎታል ይህ ካቴድራል ተሰርቶ አልቆም ላያየውም ይችላል ነገር ግን የዚህን የካቴድራል እውን መሆን ዛሬ ላይ ሆኖ በራዕይ ማየት ስለቻለ ሥራውን በትጋት እንዲሠራ ትልቅ ማበረታቻ ሆኖታል ይህም ዛሬ እያንዳንዳቸንን ራሳችንን እንድንጠይቅ ያስገድደናል? ዛሬ እኛ ምን እየገነባን ነው? ምን እየሠራን ነው?እየሠራንም ስላለው ነገር ነገ ምን አይነት ገጽታ ይኖረዋል ብሎ ማሰብ ማለም የዛሬ ሥራችንን የተቀላጠፈና ስኬታማ ከሚያደርጉት ነገሮች ዋናው ነው
ስለዚህም ራዕይ የመጨረሻው መድረሻ ምዕራፋችን ነው This is where we want our people or ourselves ahead of us. ጠቢቡ ሰሎሞን በመጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 29 ቁጥር 18 ላይ እንዲህ ይላል “ራዕይ ባይኖር ሕዝብ መረን ይሆናል Where there is no vision, the people perish. So how to figure out not to perish in the Parish is very important. ስለዚህ እንዳንጠፋ የት መሄድ እንዳለብን ወዴት እየሄድን እንደሆነ ማወቅ ግድ ይለናል ለዚህም ነው ይህ መንደርደሪያ ሐሳብ ሊቀርብ ያሰፈለገው ይህንን ለማጠናከር አንድ አጭር ታሪክ ልጨምርላችሁና ወደ ዝርዝር ነገሩ እንግባ
በአንድ ወቅት አንድ የኑሮ ውጣ ውረድ ያባዘናት አንዲት ወጣት ልጅ ስለወደፊት የኑሮዋ ዕጣ ፈንታና ዕድል እያሰበች ስትሄድ በመንታ መንገዶች ላይ ትደርሳለች በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለባት በማመንታት ላይ እንዳለች አንድ የዕድሜ ባለፀጋ የሆኑና በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ አባት ድንገት ባለችበት ቦታ ላይ ብቅ አሉ እርስዋም በደስታ ተሞልታ አባቴ ሆይ የትኛውን መንገድ ልውሰድ?በየትኛው አቅጣጫስ ልሂድ ስትል በትሕትና ጠየቀቻቸው እርሳቸውም ልጄ ሆይ መንገድ ስትጀምሪ ወዴት እሄዳለሁ ብለሽ ተነሣሽ ብለው ቢጠይቋት አባቴ ሆይ የት እንደምሄድ አላውቅም ብትላቸው እንግዲያውስ ልጄ ሆይ በየትኛውም መንገድ ብትሄጂ ለውጥ አያመጣም አልዋት ይባላል ስለዚህ እኛም የምንሄድበትን መንገድ ካላወቅን ለማወቅም ጥረት ካላደረግን የበቃ ሰው ብንጠይቅ መላእክትም ቢመጡ እራሱም እግዚአብሔርም ቢሆን የእኛ ፍላጎት ሊረዳን አይችልም እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የመምረጥ መብት የሰጠም ነው ያከብረዋልም ስለዚህ እኛ ሳንፈልግና ሳንጠይቅ በግድ ልርዳችሁ ብሎ አይመጣም ለዚህም ነው ጌታ በወንጌሉ ለምኑ ይሰጣችኋል ፈልጉ ታገኙማላችሁ መዝጊያውን አንኳኩ ይከፈትላችሁማል ያለው ማቴዎስ 7:7
Vision ራዕይ
ምዕመናን ቅድስናና የተትረፈረፈ ሕይወትን በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያገኙበት ኦርቶዶክሳዊ ማህበረሰብን መሆን። An Orthodox community where people find the abundant life and holiness in Jesus Christ.
ይህ ራዕይ የተመሠረተው በክርስቶስ ቃል ነው ዮሐንስ 10 ቁጥር 10 “ሌባው ሊሰርቅ፣ ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።”
ይህ የተትረፈረፈ ሕይወት የሚባለው ዘላለማዊ ሕይወትን ነው ግን ይህ ሕይወት የሚጀመረው በዚህ ምድር ላይ ነው በሚመጣውም የእግዚአብሔር መንግሥት ይፈጸማል ቅድስና ወይም የተቀደሰ ሕይወት እራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው 1 Peter 1:16 “Be holy for I am Holy”. 1ኛ ጴጥሮስ 1 ቁጥር 16 “ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ እንደተፃፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ” ስለዚህ ወደ ቤተ ክርስቲያን የምንመጣው ለመቀደስ ነው ቅዱሳን ለመሆን ነው ንፁሖች ለመሆን ነው ሌላው የቅድስና መገለጫ ይቅር ባዮች መሆን ነው ሉቃስ 6 ቁጥር 36 “አባታችሁ ርኅሩኅ እንደሆነ ርኅሩኆች ሁኑ” በአጠቃላይ በምድር ላይ የተጠራነው በፀጋ ትናንሽ እግዚአብሔሮችን ለመሆን ነው
Saint Athansius (298-373) said “God became man that man might become God.” ሰው በፀጋ እግዚአብሔር ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ሰው ሆነ ብሎ ታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ አትናትዮስ እንዳስተማረን
Mission Statement/የተልእኮ መግለጫ አላማውም ራዕዩን የሚተገበርበት ሥራ ማለት ነው A clear description of the fundamental purpose for which the Church exists and what it does to achieve its vision. The Mission is to have rich experiences in worship, in fellowship(Relationships), in uplifting preaching of the word and studying the Bible and in serving & witnessing for the community based on Acts 2:42
አላማችን በሐዋርያት ሥራ 2:42 ላይ በተጠቀሰው መሠረት ቅድስና የተሞላበትን የአምልኮ ሥርዓትን መፍጠር ፡ የክርስቲያኖችን ሕብረት ማጎልበት ፡ ሁለገብ ትምህርትን ማስፋፋት (መጽሐፍ ቅዱስንና የቅዱሳንን ገድል ማንበብና ማጥናት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የአኗኗር ዘይቤ) ፡ መሠረታዊ የሆነውን የቤተ ክርስቲያን ዶክትሪን ማሳወቅ :የወንጌልን ስብከት መደገፍና የወንጌልን እውነታዎች በተለያየ መንገድ ማስተላለፍ እንዲሁም ማኅበረሰባችንን መደገፍ
1.አምልኮ (Worship) 2.ክርስቲያናዊ ሕብረት (Fellowship) 3.ትምህርት (Word) 4.ማኅረሰብ (Community)
ይህንን ራዕይና ዓላማ ሊሳካ የሚችለው እራሳችንን መስቀሉን ለመሸከም የተዘጋጀን ብቻ እንደሆነ ነው ይህ የተትረፈረፈ ሕይወት ለማጣጣም መስቀሉን መሸከም የግድ ይላል በሉቃስ 14 ቁጥር 27 ላይ “ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም” ብሏል በማቴዎስ 10 ቁጥር 24 ላይ ደግሞ “ደቀ መዝሙር ከመምህሩ ባሪያም ከጌታው አይበልጥም” ሲል ጌታው እራሱ መስቀሉን ከተሸከመ ለእኛ ለደቀ መዛምርቱ የማይቀር መሆኑን በግልፅ አስቀምጦታል ስለዚህ በአጠቃላይ ይህንን ራዕይና አላማ ለማሳካትና ለመተገበር ብዙ መስዋእትነትን በሁሉ መልክ የሚጠይቅ ነው ነገር ግን በመጨረሻ ግቡ የተትረፈረፈ ሕይወትን ማግኘትና መቀደስ ነው ይህም አምላክችን ክርስቶስን መምሰል ነው
ይህ ራዕይና አላማ በአንድ ጊዜ ወይም በአጭር ጊዜ የሚተገበር አይደለም ነገር ግን ይህ ራዕይና አላማ በየጊዜው እውን እየሆነ ከሄደ ከራሳችንም አልፈን ሰፊው ማኅበረሰባችንን የምንጠቅምበት በመሆን ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልን አስተምሩ የሚለውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ትእዛዝም የምንፈጽምበት ይሆናል ቤተ ክርስቲያንን የሚያሳደገው ባለቤቱ ክርስቶስ ነው ከእኛ የሚጠበቀው በቅድስና መንገድ ላይ ሆነን መገኘት ነው ይህም በንሰሐ ሕይወት መመላለስ ማለት ነው የቤተ ክርስቲያንን እድገት ከእኛ የበለጠ የሚፈልገው እራሱ ክርስቶስ ነው ይህንንም በእነዚህ ሁለት ጥቅሶ ች እንመልከት ሉቃስ 10 ቁጥር 2 “ አላቸውም መከሩስ ብዙ ነው ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው እንግዲህ የመከሩን ጌታ ለመከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት” ስለዚህ እኛ በንፁህ ልቦና ሆነን ከጠየቅነው እድገቱ የሚመጣው በክርስቶስ ነው ማሳደግ የሚችለው እርሱ ብቻ ነው የእኛ ድርሻ በቅንነት ሆነን ሀሳባችንንና አዕምሮአችንን አገናኝተን መነሳት ብቻ ነው እንደዚሁም በማርቆስ 4 ከቁጥር 26-28 ላይ ደግሞ “እርሱም አለ በምድር ዘርን እንደሚዘራ ሰው የእግዚአብሔር መንግሥት እንደዚህ ናት ሌሊትና ቀን ይተኛል ይነሣልም እርሱም እንዴት እንደሚሆን ሳያውቅ ዘሩ ይበቅላል ያድጋልም”
ስለዚህ እግዚአብሔር ሁሌ እንድናድግ ነው የሚፈልገው ከክብር ወደ ክብር እንድንሄድ መንገዱን ከፍቷል ማደግ ካልቻልን መለወጥ ካልቻልን እንዳንራመድ የማያስቸለን አጥር (Erected barrier) አለ ማለት ነው ከእኛ የሚጠበቀው ይህንን አጥር ማፍረስ ነው እራሳችንን ያጠርንበት አጥር ሲፈርስ እድገቱ በራሱ ይመጣል ስለዚህ ጥያቄያችን ለምን አላደግንም ለምን አልተለወጥንም መሆን የለበትም ጌታችን እንደምናድግ እንደምንለወጥ ከክብር ወደ ክብር እንደምንሄድ ቃል ገብቶልናል ጥያቄያችን መሆን ያለበት ከማደግ ያቆመን ምንድን ነው ወደ እድገት እንዳንሄድ የጋረጠን ትልቁ ፍርሃት ነው ራዕያችንና አላማችን ፍርሃት ካለ ፈቀቅ አይልም ጌታችንም አትፍሩ ሲል በተለያየ ጊዜ በቅዱስ ወንጌል ውስጥ ተናግሯል
ራዕይና አላማው ስኬታማ የሚሆነው ስትራቴጂካዊ ግብ (Strategic goal) ላይ ተመሥርተን ስንቀሳንቀስ ነው ግብ ወደ ራዕዩ እና ተልዕኮው የሚወስደውን የመንገድ ካርታ ነው Goal is the road map to the Vision and mission.
Strategy is the road map of how to implement the vision and achieve the organization goals. It keeps the organization going in the right direction. ስትራቴጂው ራእዩን እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እና የድርጅቱን ግቦች ማሳካት የሚቻልበት የመንገድ ካርታ ነው ፡፡ ድርጅቱ በትክክለኛው አቅጣጫ እንዲሄድ ያደርገዋል ፡፡
Strategic goals are only as effective as the process of achieving them. ስትራቴጂካዊ ግቦች ለማሳካት የሚሄድበት ሂደት ውጤታማ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡
S.M.A.R.T. Must be specific, measurable, attainable, realistic, timeline ልዩ ፡ ሊለካ የሚችል ፡ ሊደረስበት የሚችል ፡ ተጨባጭ ፡ የጊዜ ሰንጠረዥ(ገደብ)
Specific – Is the goal specific enough for clarity so that every one will understand it? ሁሉም እንዲረዳው ግቡ ልዩ ሆኖ ግልጽ ለማድረግ በቂ ነውን?
Measurable – Is there a way to measure the success of the goal? የግቡን ስኬት ለመለካት የሚያስችል መንገድ አለ?
Attainable – Is the goal truly attainable by us within a reasonable time? ግቡ ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ እውን ሆኖ ሊደረስበት ይችላልን?
Realistic – Is the goal realistically written? ግቡ በተጨባጭ የተፃፈ ነው?
Timeline – Is there a timeline associated to the goal to ensure completion and accountability? ማጠናቀቅን እና የተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ከዓላማው ጋር የተዛመደ የጊዜ ሰንጠረዥ አለ?
Lack of strategic planning is the barrier for us to growing in holiness and live out the abundant life Christ already gave us. የስትራቴጂካዊ እጦትና እጥረት ቅድስናን እንዳንቀናጅ እና ክርስቶስ የሰጠንን የተትረፈረፈ ሕይወት እንዳይኖር እንቅፋት ነው ፡፡ Strategic planning is our process to define our direction (Strategy) and allocate our resources to achieve our goals.
The strategic plan must answer four fundamental questions.
- Why do we exist? We must be able to articulate why should anyone want to be part of our Church and Why our Church matters? ለምን እንደ ቤተ ክርስቲያን አለን? ሁላችንም የቤተክርስቲያናችን አባል መሆን የሚፈልግ እና ለምን ቤተክርስቲያናችን ጋር መሆን አስፈላጊ እንደሆነ መግለጽ መቻል አለብን።
- Where are we now? Brutal facts አሁን በምን ደረጃ ላይ ነው ያለነው
- Where do we want to be? ምን ደረጃ ላይ መድረስ እንፈልጋለን
- How do we get there? Were specific activities are outlined in each strategic area of focus? እዚያ እንዴት እንደርስ? በእያንዳንዱ የትኩረት መስክ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎች ተዘርዝረዋል?
እያንዳንዱ ስትራቴጂ ግን ከተልእኮ ጋር እየተገናኘ ራዕዩን ያሳካል
- Worship አምልኮ
- ቅዳሴውን ማስተማር Liturgy walk-through sessions (Classes) ተቀድቶ በአጭር በአጭሩ ቢሠራ
- ቅዳሴ መጽሐፉ በአማርኛ በእንግሊዘኛና በእንግሊዘኛ አናባቢ ቢታተም
- በቅዳሴ ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ሥርዓቶችን በተለያየ መልኩ ማስተማር
- Screen በቤተ ክርስቲያኑ ሁሉ ለምዕመናኑ እንዲታይ ማድረግ
- ቤተ ክርስቲያን ውስጥም ሆነ ውጭ ማስዋብና ንፅህናውን መጠበቅ (Altar screen, Icons, Curtains, waiting area, bathrooms)
2. ክርስቲያናዊ ሕብረት (Fellowship)
- በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሰንበቴ ማኅበራትን ማደራጀትና ማበረታታት
- የንግግር የምክክር የጥያቄና መልስ የምስክርነት ዝግጅት ማዘጋጀት
- Picnic (ሽርሽር) በቤተ ክርስቲያን ደረጃ ቢያንስ በአመት አንድ ጊዜ ማዘጋጀት
- Retreat (መንፈሳዊ ጉዞ) የቀንም ሆነ የአዳር በተለያዩ ማኅበራት (የሴቶች ፡ የወንዶች ፡ የወጣቶች ፡ የቤተሰብ)ማዘጋጀት
- የፅዋ ማኅበራትን ማበራራትና መደገፍ
3. ትምህርት (Word)
- የወንጌልን ስብከትን በተለያየ መልኩ ማስፋፋት (በጽሑፍ በቪድዮ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት)
- የቅዱሳን ገድል እንዲነበብ በተለያየ መልኩም ለምዕመናኑ ማስተዋወቅ
- ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ማስተማር
- ክርስቲያናዊ የአኗኗር ዘይቤን በተለያየ መልኩ በማስተማር ምዕመናን ላይ እንዲሠርጽ ማድረግ
4. ማኅረሰብ (Community)
- የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማኅበረሰቡ ማስፋፋት
- Prison ministry, Helping the elderly, Single mothers, food bank, feeding the hungry
Organizational Chart ወጥቶ እያንዳንዱ ኮሚቴ እንዴት ወይንም በምን መልኩ ከሰበካ ጉባኤው ጋር እንዲገናኝና እያንዳንዱ ኮሜቴ ሥራው defined ሆነ መመሪያ ያስፈልገዋል በአጠቃላይ ግቡ እንዲሳካ ያለው ተጨባች ሁኔታው እየታየ በየጊዜው እየተሻሻለ ከተሠራ ለቤተ ክርስቲያናችን አመርቂ ውጤት ያስገኛል ይህ እንደመርደርደሪያ ሀሳብ ብቻ የቀረበ ሀሳብ ስለሆነ እውቀት ያላቸው ካህናትና ምዕመናን የሚቀነሰውን ቀንሰው የሚጨመረውን ጨምረው እንዲያሻሽሉት ያስፈልጋል
ወስብሐት ለእግዚአብሔር